በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች

1. በዚህ የማስታወቂያ ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ ስካን ማድረግ የሚቻለው የትኛው የ Double A  ምርት ላይ ያለውን QR ኮድ ነው?
መልስ ፡ በዚህ የማስታወቂያ ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ ስካን ማድረግ የሚቻለው Double A 80gsm A4 size የህትመት ወረቀትን ብቻ ነው፡፡
2. የ QR ኮዱ የሚገኘው የት ጋር ነው?
መልስ ፡ የ QR ኮዱ የሚገኘው በ Double A 80gsm A4 የካርቶን ክዳን ላይ በውስጥ በኩል ነው፡፡
3. ፕሮግራሙ የሚቆየው ከመቼ እስከ መቼ ነው?
መልስ ፡ ፕሮግራሙ የሚቆየው፡ ከ ከመስከረም 14, 2016 እስከ ታህሳስ 14, 2016
4. በዚህ የማስታወቂያ ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ አንድ ተሳታፊ ማሟላት ያለበት መስፈርት ምንድን ነው?
መልስ ፡ በዚህ የማስታወቂያ ፕሮግራም ላይ መሳተፍ የሚፈልግ የ Double A ምርት ተጠቃሚ ፤ እድሜው 18 ዓመት እና ከዛ በላይ ፤ ኢትዬጵያዊ ወይም ኢትዬጵያ ውስጥ ነዋሪ የሆነ መሆን ያለበት ሲሆን ስጦታዎችን ለትክክለኛ አሸናፊዎች ለመስጠት ይረዳ ዘንድ በምዝገባ ወቅት ተሳታፊው እንዲያስገባ የሚጠየቁ መረጃዎችን በትክክል ማስገባት ይኖርበታል፡፡
5. የ QR ኮድ ስካን ነጥብ የሚመዘገበው እንዴት ነው?
በዚህ የማስታወቂያ ፕሮግራም ወቅት አንድ ተሳታፊ አንድ የመለያ ቁጥር የሚሰጠው ሲሆን በ Double A 80gsm A4 የካርቶን ክዳን ላይ በውስጥ በኩል ያለውን የ QR ኮድ ስካን በማድረግ ነጥቦች መሰብሰብ ይችላል፡፡ አንድ QR ኮድ ስካን አንድ ነጥብ ይይዛል፡፡ አንድ ሰው አንድን የ QR ኮድ ስካን ማድረግ የሚችለው አንድ ጊዜ ብቻ ሲሆን አንድ QR ኮድም ስካን መደረግ የሚችለው በአንድ ተሳታፊ ብቻ ነው፡፡
6. ስካን በማረግበት ጊዜ ለምንድን ነው “መቀጠል አይችልም እባክዎ እንደገና ይሞክሩ” የሚል መልዕክት የሚያሳየው?
ይህ መልክት የሚመጣው አንድ ተሳታፊ አንድን የ QR ኮድ በተደጋጋሚ ስካን ለማድረግ ሲሞክር ወይም በሌላ ሰው ስካን የተደረገን ካርቶን በድጋሚ ስካን ለማደረግ ሲሞክሩ ነው፡፡ ተደጋጋሚ ሰካን የተደረገ ኮድ በሚገኝበት ጊዜ ድርጂቱ ያለምንም ማሳወቂያ ተደጋግመው ስካን የተደረጉ ኮዶችን በመተው መጀመርያ ስካን የተደረገውን 1 ነጥብ በቻ ይመዘግባል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ www.doublearewards.com/ethiopia ድህረ ገፅ ይጎብኙ፡፡
7. ተሳታፊው የሞባይል ቀፎውን ቢቀይር እንደገና መመዝገብ አለበት?
የተሳታፊው መለያ ቁጥር የሚያያዘው ከስልክ ቁጥሩ ጋር ስለሆነ የስልክ ቀፎ መቀየሩ ድጋሜ እንዲመዘገብ አያስገድደውም፡፡ ነገር ግን የስልክ ቁጥሩን ከቀየረ ተሳታፊው እንደገና መመዝገብ ይኖርበታል፡፡
8. አንድ ተሳታፊ በሰበሰበው ነጥብ የሞባይል ካርድ ከወሰደ በኃላ ይህንኑ ነጥብ ተጠቅሞ ብሄራዊ ሎተሪ በሚደረገው እድለኞችን የመለየት የእጣ ማውጣት ስነስርአት ላይ ተሳታፊ በመሆን እድል ይኖረዋል ወይ?
መልስ ፡ አዎ ይኖረዋል፡፡ 
9. በዚህ ፕሮግራም ላይ አንድ ተሳታፊ ስጦታዎችን እና ሽልማቶችን ስንት ግዜ ማግኘት ይችላል
መልስ ፡ በዚህ ፕሮግራም ላይ አንድ ተሳታፊ በመረጠው ደረጃ አንድ ግዜ ብቻ የሞባይል ካርድ ስጦታ ማግኘት የሚችል ሲሆን ይኼው ተሳታፊ ከሞባይል ካርድ ስጦታው በተጨማሪ ይኼንኑ የሰበሰበውን ነጥብ ተጠቅሞ ብሄራዊ ሎተሪ በሚደረገው እድለኞችን የመለየት የእጣ ማውጣት ስነስርአት እድለኛ የሆነ እንደሁ ሽልማት መውሰድ የሚችለውም አንድ ግዜ ብቻ ይሆናል፡፡
10. በተቀመጠው መስፈርት መሰረት የ QR ኮድ ስካን ያደረገ ተሳታፊ ስጦታዎችና ሽልማቶችን መውሰድ የሚቻለው እንዴት ነው?
መልስ ፡ የሞባይል ካርድ ስጦታዎችን በመረጠው ደረጃ የተቀመጠውን የ QR ኮድ ብዛት ስካን ካደረገ በኃላ ስልኩ ላይ በጫነው አፕልኬሽን ወዲያውኑ የሞባይል ካርድ ስጦታውን መውሰድ የሚችል ሲሆን ብሄራዊ ሎተሪ በሚደረገው እድለኞችን የመለየት የእጣ ማውጣት ስነስርአት እድለኛ የሆነ እንደሆን ሽልማቱን በስልክ መልእክት መይም በስልክ ጥሪ በሚነገረው አድራሻ መሰረት ሽልማቱን በአካል ቀርቦ መውሰድ ይችላል፡፡ እድለኛው ጥሪው በደረሰው በ 6 ወር ውስጥ ሽልማቱን ካልወሰደ ድርጅቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
11. ስጦታዎቹና ሽልማቶቹ ምን ምን ናቸው?
በዚህ የማስታወቂያ ፕሮግራም ላይ ሁለት አይነት ማለትም ስጦታዎች እን ሽልማቶች ሲኖሩ፡
ሀ. ስጦታዎች ፡ ነጥቦችን በመሰብሰብ ስልኮ ላይ በጫኑት አፕልኬሽን ወዲያውኑ የሞባይል ካርድ ስጦታ ማግኘት የሚችሉበት ሲሆን መሰብሰብ ያለብዎ ነጥብና ማግኘት የሚችሉት የሞባይል ካርድ ስጦታ መጠን ከታች በስንጠረዥ እንደተቀመጠው ይሆናል፡፡
ደረጃዎች ስካን ብዛት ስጦታዎች
ደረጃ 1 1 ካርቶን የ 50 ብር የሞባይል ካርድ
ደረጃ 2 4 ካርቶን የ 100 ብር የሞባይል ካርድ
ደረጃ 3 25 ካርቶን የ 500 ብር የሞባይል ካርድ
ለ. ሽልማቶች ፡ በሰበሰቡት ነጥብ መሰረት እድለኞችን ለመለየት ብሄራዊ ሎተሪ በሚደረገው የእጣ ማውጣት ስነስርአት ላይ በቀጥታ ተሳታፊ በመሆን እድልዎን እንዲሞክሩ የሚያስችል ዘርፍ ሲሆን በዚህም መሰረት አንድ ተሳታፊ የማሸነፍ እድሉን ለማስፋት ይረዳው ዘንድ ያለገደብ እስካን ማረግ ይችላል፡፡ በዚህ ዘርፍ ለሽልማትነት የቀረቡ እቃዎች ዝርዝር እና ብዛት ከታች በሰንጠረዥ እንደተቀመጠው ይሆናል፡፡
የሽልማት አይነቶች መለኪያ ብዛት
ስማርት ስልክ (Iphone 14 Pro Max, 128GB) ብዛት 6
ላፕቶፕ (HP i5 11th generation, 8GB ram, 215GB SSD) ብዛት 9
ቲቪ (Flat Screen 55'') - LG ብዛት 3
የልብስ ማጠብያ ማሽን - West Point ብዛት 9
የውሀ ማጣሪያ - West Point ብዛት 9
ማይክሮ ዌቭ ኦቨን - West Point ብዛት 9
ታላቁ ሽልማት - ወርቅ, 75ግራም, 21K በግራም 75
ተጨማሪ ጥያቄ ካለዎት እባክዎ በ EthiopiaQR@doublea1991.com  የኢሜይል አድራሻ ይጻፉልን፡፡