ህጎች እና ሁኔታዎች

Double A QR Lucky Draw and Point Collection 2023 ፕሮግራም በኢትዮጵያ

  1. 1. የ QR Lucky Draw and Point Collection ፕሮግራም እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ከመስከረም 14, 2016 እስከ ታህሳስ 14, 2016 ይቆያል፡፡
  2. 2. ፕሮግራሙ የተዘጋጀው በ Double A (1991) Public Company Limited እና በአጋሮቹ ነው።
  3. 3. በፕሮግራሙ ለመሳተፍ የተመዘገበ ተሳታፊ ("ተሳታፊው")፡-
    1. a. የ Double A ወረቀት ተጠቃሚ መሆን አለበት
      b. ቢያንስ 18 አመት እድሜ ያላቸው ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች እና በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲዊ ሪፑብሊክ ግዛት ውስጥ ብቻ ነዋሪ መሆን አለባቸው፡፡
  4. 4. ተሳታፊዎች በ Double A ካርቶን ክዳን ስር የሚገኘውን የ QR ኮድ ስልካቸው ላይ በሚጭኑት የ Double A QR መተግበርያ (አፕልኬሽን) ስካን ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ የ Double A ካርቶን ሲባል 80 GSM ፤ A4 ፣ 5 ደስታ/ካርቶን ፤ 500 ቅጠል/ደስታ ሆኖ የታሸገ ማለት ነው፡፡ ተሳታፊዎች Double A QR መተግበርያን ስላካቸው ላይ ከጫኑ በኃላ ስም፣ የአባት ስም፣ ስልክ ቁጥር፣ ከተማ ፣ የልደት ቀን ፣ ኢ-ሜል ፣ የድርጅቱን ስም እና ወረቀቱን ለግል ወይም ለድርጅት እንደሚጠቀሙ የሚሞላ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ለግል ወይም ለድርጅት ግልጋሎት መሆኑን የሚገለፅ ሲሆን ለድርጅት ግልጋሎት የሚውል ከሆነ ተሳታፊዎች የድርጅቱን ስም ሙሉ በሙሉ የሚገልፁ እና በመቀጠል ተሳታፊዎች ለፕሮግራሙ ቆይታ ውስጥ አንድ የሎቶ ቁጥር የሚኖራቸው ይሆናል፡፡
  5. 5. የ Point Collection ፕሮግራም ከ Lucky Draw ፕሮግራም ጋር በተመሳሳይ ወቅት ይተገበራል።
  6. 6. ተሳታፊዎች አንድን የ QR ኮድ አንድ ጊዜ ብቻ ስካን ማድረግ የሚችሉ ሲሆን አንድ የ QR ኮድ ለ አንድ ተሳታፊ ብቻ ያገለግላል። በ 2021እና 2022 ተመሳሳይ ፕሮግራሞች ስካን የተደረጉ የ QR ኮዶች በ አሁኑ ፕሮግራም አገልግሎት የላቸውም።
  7. 7. ድርጅቱ መደበኛ ያልሆነ ስካን ከለየ ይኸውም ተመሳሳይ QR ኮድ ቁጥር በአንድ ግለሰብ ተሳታፊነት ለበርካታ ጊዜያት (1 QR ኮድ ቁጥር ከ1 ጊዜያት በላይ ስካን ሲደረግ) ድርጅቱ ይህንን ግለሰብ ያለቅድመ ማሳሰቢያ ውደቅ የማድረግ መብት የሚኖረው ሲሆን ይህም በተሳታፊው ያልተገባ ተሳትፎ ምክንያት በመሆኑ ነው፡፡
  8. 8. ተሳታፊዎች ነጥብ ለመሰብሰብ በ Double A ካርቶን ክዳን ስር የሚገኘውን የ QR ኮድ ስካን ማድረግ ይስችላሉ።
  9. 9. 1 የ QR ኮድ = 1 ነጥብ
  10. 10. በፕሮግራም ጊዜው ውስጥ ተሳታፊዎች Lucky Draw ሽልማትን ለማሸነፍ የሚኖራቸው አንድ እድል ብቻ ይሆናል።ድርጅቱ ከብሄራዊ ሎተሪ ጋር በመተባበር በነሲብ በሚወጣ እጣ አሸናፊዎችን የሚለይ ሲሆን እጣውም እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ጥቅምት 20, 2016/ህዳር 21, 2016/ታህሳስ 21, 2016 በአጠቃላይ በፕሮግራሙ ቆይታ ግዜ ውስጥ ለ 3 ጊዜያት እጣ የሚያወጣ ይሆናል፡፡ ይህ የዕጣ ማውጣት መርሃ ግብር ሊተነበዩ በማይችሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ምክንያት ሊለወጥ ይችላል።
  11. 11. በ 1ኛው ዙር የ Lucky Draw እጣ አወጣጥ የተካተተ ነጥብ በ 2ኛው ና በ3ኛው ዙር የ Lucky Draw እጣ አወጣጥ አይካተትም። በተጨማሪም በ 2ኛው ዙር የ Lucky Draw እጣ አወጣጥ የተካተተ ነጥብ በ3ኛው ዙር የ Lucky Draw እጣ አወጣጥ አይካተትም። ነገር ግን ሁሉም በ 1ኛ፣ 2ኛ ን 3ኛ ዙር የተሰበሰቡ ነጥቦች በ3ኛው ዙር ለሚካሄደው ከፍተኛ ሽልማት በሚያስገኘው (ማለትም የ 75 ግራም ወርቅ ሽልማት) እጣ ውስጥ እንደገና እንዲሳተፉ ይደረጋል፡፡
  12. 12. የ Lucky Draw ሽልማቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡፡ እነዚህም፡-
  13. የ Lucky Draw ሽልማቶች የ Lucky Draw ሽልማቶች ብዛት
    ስማርት ስልክ (iPhone 14 Pro Max, 128GB Storage) በፍሬ 6
    ላፕቶፕ (HP i5 11th generation, 8GB ram, 512GB SSD) በፍሬ 9
    ቲቪ (ፍላት ስክሪን 55 ኢንች) – LG በፍሬ 3
    የልብስ ማጠቢያ ማሽን (West Point) በፍሬ 9
    የውሃ ማጣሪያ (West Point) በፍሬ 9
    ማይክሮዌቭ ኦቨን (West Point) በፍሬ 9
    ከፍተኛ ሽልማት - ወርቅ 75 ግራም ፣ 21 ካራት ግራም 1
  14. 13. በአጠቃላይ ተሳታፊዎች የ Point Collection ስጦታዎችን በፕሮግራሙ ጊዜ ወስጥ አንድ ጊዜ ብቻ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን የተዘጋጁትን የሞባይል ካርድ ስጦታዎች Double A QR መተግበሪያን በመተቀም ወዲያውኑ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን ተሳታፊዎች የ Lucky Draw ሽልማቶችን ለማሸነፍ ሰፊ እድል እንዲኖራቸው እስከቻሉት መጠን QR ኮድ ስካን ማድረግ ይችላሉ፡፡
  15. 14. የ Point Collection ሽልማቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡፡ እነዚህም፡-
  16. ደረጃዎች ዝቅተኛ የስካን መጠን ነጥብ አሰባሰብ ሞባይል ካርድ ስጦታ የስጦታዎች ብዛት
    ደረጃ 1 ስካን 1 QR ኮድ 1 ነጥብ ያገኛል ባለ 50 ብር የመጀመርያዎቹ 6000 ተሳታፊዎች ብቻ የስጦታዎቹ አሸናፊ ይሆናሉ
    ደረጃ 2 ስካን 4 QR ኮድ 4 ነጥብ ያገኛል ባለ 100 ብር የመጀመርያዎቹ 5500 ተሳታፊዎች ብቻ የስጦታዎቹ አሸናፊ ይሆናሉ
    ደረጃ 3 ስካን 25 QR ኮድ 25 ነጥብ ያገኛል ባለ 500 ብር የመጀመርያዎቹ 1000 ተሳታፊዎች ብቻ የስጦታዎቹ አሸናፊ ይሆናሉ
  17. 15. የ Lucky Draw ሽልማቶችን ያሸነፉ ተሳታፊዎች ሽልማታቸውን ለመውሰድ አዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ ቦሌ መድሀኒአለም አካባቢ ወረዳ 03 ዋንዛ ህንጻ 7ኛ ፎቅ በ ሚገንኛው ቤሪ አድቨርታይዚንግቢሮ መገኘትና የሚከተሉትን መረጃዎች ማሟላት አለባቸው።
    1. a. ስማቸውን የሚገልፅ ብሔራዊ የመታወቂያ ካርድ ወይም ፓስፖርት ወይም ማንኛውም ሌላ ህጋዊ ተቀባይነት ያለው መታወቂያ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ይኸውም ሽልማቱን ለመቀበላቸው በማስረጃነት እንዲያገለግል በ Double A QR አፕሊኬሽን ውስጥ ካስመዘገቡት ዝርዝር መረጃ ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
      b. ለማስረጃነት እንዲረዳ በስልካቸው በ Double A QR አፕሊኬሽን ስጦታዎችን የወሰዱበትን ማሳየት አለባቸው።

    ተሳታፊዎች ወደ ማስታወቂያ ድርጂቱ ከመምጣታቸው በፊት ያሸነፉትን ሽልማት በ Double A QR አፕሊኬሽን ሪዲም ማድረግ አለባቸው። ከላይ የተጠቀሱት ማስረጃዎች ያልተሟሉ ከሆነ ድርጅቱ ከአሸናፊነት ለማወጅ ውድቅ ሊያደርጋቸው የሚችል እና ሽልማቶችን ላለመስጠት መብት የሚኖረው ይሆናል፡፡ አሸናፊዎች ሽልማታቸውን በድርጅቱ በተገለፀው ቀንና ሰዓት መወሰድ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ እና በቀጣዩ ስድስት ወራት ውስጥ ሽልማታቸውን ካልተረከቡ መብቱ ተላልፎ እንደተሰጠ ሆኖ ይቆጠራል፡፡
  18. 16. ሽልማቶችን ያሸነፉ ተሳታፊዎች ሽልማታቸውን፤ በ Double A QR መተግበሪያ በሚጠቀሰው ቀንና ሰዐት መውሰድ አለባቸው።
  19. 17. የፕሮግራሙ መርሃ ግብር ሊተነበዩ በማይችሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ምክንያት ሊለወጥ ይችላል። የመርሀግብር ለውጦቹንም ድርጅቱ በ www.doublearewards.com/ethiopia ድረገፅ ወይም በማህበራዊ ገጻችን www.facebook.com/doubleaethiopia ላይ ያሳውቃል፡፡
  20. 18. ምናልባት በኢትዮጵያ ህግ የተከለከሉ ሁኔታዎች ካሉ በአገሪቱ ባሉት ህግጋት መሰረት መስተካከል ይችላሉ ይሁንና ሌሎቹ ሁኔታዎች በምንም መንገድ መለወጥ ወይም ሥራ ላይ እንዳይውሉ መደረግ የለባቸውም፡፡
  21. 19. ከስር በተቀቅመጠው ወርሃዊ ኮታ መሰረት ተሳታፊዎች የ QR ኮዶችን ስካን በማድረግ የ Point Collection ስጦታዎችን ማግኘትና እና ነጥቦችን መሰብሰብ ይችላሉ፡፡ ከዚህ በታች ባለው ሠንጠረዥ እንደሚታየው ወርሃዊ ስጦታዎችን ለማግኘት ብቁ የሚሆኑት ከወርሃዊው ኮታ ጋር እኩል ቁጥር ያላቸው የመጀመሪያዎቹ ተሳታፊዎች ብቻ ናቸው።
  22. ደረጃዎች ሞባይል ካርድ ስጦታ 1ኛ ዙር 2ኛ ዙር 3ኛ ዙር ጠቅላላ
    ደረጃ 1 ባለ 50 ብር 1,000 3,000 2,000 6,000
    ደረጃ 2 ባለ 100 ብር 500 3,000 2,000 5,500
    ደረጃ 3 ባለ 500 ብር 250 500 250 1,000
    ጠቅላላ 1,750 6,500 4,250 12,500



    የ QR Lucky Draw and Point Collection ፕሮግራም በኢትዮጵያ ሁኔታዎች

    1. 1. መግቢያ
      1. 1.1. እነዚህ ውሎች እና ሁኔታዎች በ Double A (1991) Public Company Limited እና በአጋሮቹ ለተዝጋጀው የ Double A QR Lucky Draw and Point Collection ፕሮግራም መመሪያዎች ናቸው።
        1.2. የ QR Lucky Draw and Point Collection ፕሮግራም እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ከመስከረም 14, 2016 እስከ ታህሳስ 14, 2016 ይቆያል፡፡
        1.3. በፕሮግራሙ ለመሳታፍ የተመዘገቡ ተሳታፊዎች ለ ፕሮግራሙን ህጎች እና ሁኔታዎች ተገዢ መሆን ይኖርባቸዋል።
        1.4. ድርጅቱ ሽልማቶች ውስጥ ለመሳተፍ ህጎችን እና ሁኔታዎችን የመለወጥ መብት ይኖረዋል፡፡ እነዚህ ለውጦች በ(www.facebook.com/DoubleAEthiopia) እና (www.doublearewards.com/ethiopia) የሚያሳውቅ ይሆናል፡፡
        1.5. ድርጂቱ ፕሮግራሙን በራሱ ፈቃድ በማንኛውም ጊዜ ሊያቆም ይችላል።
        1.6. ከተሳትፎ ጋር በተያያዙ ህጎች እና ሁኔታዎች ለሚፈጠሩ ጥያቄዎች ወይንም አለመግባባቶች የ ድርጂቱ ውሳኔ የምጨረሻ ይሆናል።
    2. 2. ተሳትፎ
      1. 2.1. ተሳታፊዎች በ Double A ካርቶን ክዳን በውስጥ በኩል የሚገኘውን የ QR ኮድ ስልካቸው ላይ በሚጭኑት የ Double A QR መተግበርያ (አፕልኬሽን) ስካን ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ የ Double A ካርቶን ሲባል 80 GSM ፤ A4 ፣ 5 ደስታ/ካርቶን ፤ 500 ቅጠል/ደስታ ሆኖ የታሸገ ማለት ነው፡፡ ተሳታፊዎች Double A QR መተግበርያን ስላካቸው ላይ ከጫኑ በኃላ መተግበሪያው የሚጠይቀውን መረጃዎች በትክክል ማስገባት ይኖርባቸዋል። ፕሮግራሙ ካለቀ በኋላ መመዝገብ ተቀባይነት አይኖረውም።
        2.2. ተሳታፊዎች የፕሮግራሙን ህጎች እና ሁኔታዎች ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ተሳታፊዎች የ Double A QR መተግበርያ አውርደው ለተሳትፎ ምዝገባ ዝርዝር መረጃዎችን ሲሞሉና በ Double A ካርቶን ክዳን በውስጥ በኩል የሚገኘውን የ QR ኮድ ስካን ሲያደርጉ በዚህ ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ እና በሁሉም ረገድ ሽልማቶችን ለመቀበል የሚያስፈልጉ ህጎችን እና ሁኔታዎችን እንደተቀበሉ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
        2.3. ድርጂቱ ተሳታፊዎች ያልትሟላ መረጃ ወይም የተሳሳተ መረጃ በሚያስገቡበት ውቅት፤ እንዲሁም ውሎችና ሁኔታዎች ሳይከበሩ ሲቀሩ የተሳታፊዎች ተሳትፎ ሊያቋርጥ ይችላል።
    3. 3. ብቁነት / ብቁ አለመሆን
      1. 3.1. ለተሳትፎ ብቁ ለመሆን፦
          3.1.1. ቢያንስ 18 አመት እድሜ ያላቸው ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች እና በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲዊ ሪፑብሊክ ግዛት ውስጥ ብቻ ነዋሪ መሆን አለባቸው፡፡
          3.1.2. የ Double A ወረቀት ተጠቃሚ መሆን አለበት
        3.2. የ Double A (1991) Public Company Limited እና አብረው የሚሰሩ ድርጅቶች ማለትም አስመጭዎች፤ አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች፤ የማስታወቂያ ደርጅቶች ሰራትኞች/እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው/ ለተሳትፎ ብቁ አደሉም።
        3.3. ከላይ 3.2 በተጠቀሰው መሰረት በአከፋፋዮችና ለሎች ደንበኞች ላይ ላይ ለፕሮግራሙ ዋና ተጠቃሚዎችን የመገምገም እና የማረጋገጥ እና በተሳታፊው ተሳትፎን የመከልከል ወይም የማቋረጥ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
    4. 4. ከፕሮግራሙ ስለመታገድ
      1. 4.1. ድርጂቱ ከስር በጠቀሰው መሰረት ተሳታፊውን በማንኛውም የፕሮግራሙ ደረጃ ውድቅ የማድረግ እና/ወይም ሽልማቱን የመሻር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፟
          4.1.1. ተሳታፊው ብቁ ካልሆነ ወይም ሁሉንም የብቃት መስፈርቶች ካላሟላ
          4.1.2. ተሳታፊው ውሎቹን እና ሁኔታዎችን ወይም ማንኛውንም የሚመለከተውን ህግ ወይም ደንብ ከጣሰ
          4.1.3. ድርጂቱ ተሳታፊው በማጭበርበር, ወይም በማታለል የፕሮግራሙን አሠራር ለማዳከም ሞክሯል ብሎ ካመነ.
    5. 5. ነጥብ አሰባሰብ
      1. 5.1. ተሳታፊዎች በ Double A ካርቶን ክዳን ስር የሚገኘውን የ QR ኮድ ስልካቸው ላይ በሚጭኑት የ Double A QR መተግበርያ (አፕልኬሽን) ስካን ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ 1 QR ኮድ ሰካን ሲያደርጉ 1 ነጥብ ያገኛሉ።
        5.2. ተሳታፊዎች አንድን የ QR ኮድ አንድ ጊዜ ብቻ ስካን ማድረግ የሚችሉ ሲሆን አንድ የ QR ኮድ ለ አንድ ተሳታፊ ብቻ ያገለግላል። በ 2021እና 2022 ተመሳሳይ ፕሮግራሞች ስካን የተደረጉ የ QR ኮዶች በ አሁኑ ፕሮግራም አገልግሎት የላቸውም።
    6. 6. ሽልማቶች
      1. 6.1. ድርጂቱ በ (www.facebook.com/DoubleAEthiopia) እና www.doublearewards.com/ethiopia ) በሚያሳውቀው መሰረት ሽልማቶችን ያሸነፉ ተሳታፊዎች ሽልማታቸውን መውሰድ ይችላሉ።
        6.2. ተሳታፊዎች የ point collection ስጦታዎችን ማለትም የሞባይል ካርድ ሰጦታዎችን፤ የሚፈለገውን ነጥብ በሟሟላት መውሰድ ይችላሉ።
        6.3. በአጠቃላይ ተሳታፊዎች የ Point Collection ስጦታዎችን በፕሮግራሙ ጊዜ ወስጥ አንድ ጊዜ ብቻ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን የተዘጋጁትን የሞባይል ካርድ ስጦታዎች Double A QR መተግበሪያን በመተቀም ወዲያውኑ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን ተሳታፊዎች የ Lucky Draw ሽልማቶችን ለማሸነፍ ሰፊ እድል እንዲኖራቸው እስከቻሉት መጠን QR ኮድ ስካን ማድረግ ይችላሉ፡፡

        በፕሮግራም ጊዜው ውስጥ ተሳታፊዎች Lucky Draw ሽልማትን ለማሸነፍ የሚኖራቸው አንድ እድል ብቻ ይሆናል።ድርጅቱ ከብሄራዊ ሎተሪ ጋር በመተባበር በነሲብ በሚወጣ እጣ አሸናፊዎችን የሚለይ ሲሆን እጣውም እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ጥቅምት 20, 2016/ህዳር 21, 2016/ታህሳስ 21, 2016 በአጠቃላይ በፕሮግራሙ ቆይታ ግዜ ውስጥ ሶስት ጊዜያት እጣ የሚያወጣ ይሆናል፡፡ ይህ የዕጣ ማውጣት መርሃ ግብር ሊተነበዩ በማይችሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ምክንያት ሊለወጥ ይችላል።
        6.4. ድርጅቱ ሽልማቱን በተመሳሳይ ወይም እኩል ዋጋ በሚይዝ ሽልማት የመቀየር መብት አለው፡፡
        6.5. ሽልማቶቹ ለተሳታፊዎች ከተላለፉ በኋላ ቢጎዱ፤ ወይም ቢሰረቁ ድርጂቱ ሃላፊነት አይወስድም።
        6.6. ድርጅቱ ለሽልማት ጥራት ሃላፊነትን አይወስድም፡፡ የሽልማቱን የጥራት ማረጋገጫ፣ በአምራች ሻጭ እና አገልግሎት አቅራቢ ይወሰናል፡፡
        6.7. ሽልማት ያሸነፈ ተሳታፊ ለሌላ ግለሰብ ሸልማቱን የመውሰድ መብት ማስተላለፍ አይችልም።
    7. 7. የሽልማት አወሳሰድ
      1. 7.1. ሽልማት ያሸነፈ ተሳታፊ ማስታወቂያ ድርጅቱ በኩል በስልክ ጥሪ አልያም አጭር የስልክ መልእክት ሽልማቱን እንዲወስድ የሚነገረው ሲሆን ሽልማት የሚሰጥበት ቦታ፤ ሰዓትና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች በዚያው እንዲያውቅ ይደረጋል።
        7.2. በ ቁጥር 7.1. በተቀመጠው መሰረት ሽልማት ያሸነፈ ተሳታፊ ጥሪ እንደቀረበለት ሽልማቱን ቦሌ ክ/ከተማ ቦሌ መድሀኒአለም አካባቢ ወረዳ 03 ዋንዛ ህንጻ 7ኛ ፎቅ በ ሚገኘው ቤሪ አድቨርታይዚንቢሮ በመገኘት የፕሮግራሙ ጊዜ ከማለቁ በፊት ወይም ፕሮግራሙ ካለቀበት ቀን ጊዜ ጀምሮ በ 6 ወር ጊዜ ውስጥ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ3 ሰዓት እስከ 5፡30 ወይም ከሰአት ከ7፡00 እስከ 10፡00 ሰአት ድረስ ሽልማቱን መቀበል ይችላል፡፡
        7.3. ቅዳሜ ፤ እሁድ እና የህዝብ በአላቶች በስተቀር አሸናፊዎች ሽልማታቸውን ለመቀበል ከመምጣታቸው ቢያንስ ከሁለት ቀናት በፊት በማስቀደም ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
        7.4. አሸናፊው በ ቁጥር 7.1. እንደተጠቀሰው ሽልማቱን ለመቀበል በሚመጣበት ግዜ ከስር የተጠቀሰውን ማስርጃ ማቅረብ ይጠበቅበታል። ከስር በተገለፀው ውስጥ ማንኛውም ማስረጃ ያልተሟላ ከሆነ ውድቅ እንደሆነ ተደርጎ የሚቆጠር እና ሽልማቱ የማይሰጥ ይሆናል፡፡
          7.4.1. ብሔራዊ የመታወቂያ ካርድ ወይም ፓስፖርት ወይም ማንኛውም ሌላ ህጋዊ ተቀባይነት ያለው መታወቂያ ካርድ ዋናውና ኮፒውን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
        7.5. አሸናፊው ሽልማቱን ራሱ መቀበል የማይችል ከሆነ አሸናፊዎች ተወካይ በመወከል በእነርሱ በኩል ልማቱን ለመቀበል የውክልና ስልጣን ለተወካይ የሚሰጡ ሲሆን ተወካዩ የአሸናፊውን ብሔራዊ መታወቂያ ካርድ ቅጂ ከተረጋገጠ ትክክለኛ ቅጂ እና ዋና የተወካዩ ግለሰብ መታወቂ ካርድ ጋር በማስረጃነት ያቀርባል፡፡
        7.6. በተገለፀው ቀን እና ጊዜ ማለትም እጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ስድስት ወራት ውስጥ ሽልማቶቹን ለመቀበል ግለሰቡ ካልመጣ መብቱን እንደተወ ተደርጎ የሚወሰድ እና ሽልማቱን ለመቀበል እንደማፈልግ የሚቆጠር ይሆናል፡፡ በመሆኑም ድርጅቱ ሽልማቱን ለተጠባባቂ አሸናፊ የመስጠት መብት ይኖረዋል፡፡ ተጠባባቂ አሸናፊ ከሌለ ድርጅቱ ሽልማቶችን የማይሸልም እና ከቀጣዩ እጣ ጋር የማያገናኘው ይሆናል፡፡
    8. 8. መረጃ አሰባሰብ
      1. 8.1. ድርጅቱና የድርጅቱን አጋሮች ወይም ወኪሎች ከተሳታፊዎች ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ማለትም የተሳታፊ ስም፤ ያባት ስም ፤ ስልክ ቁጥር፤ መኖሪያ አድራሻ እንዲሁም ኩኪዋች ለሚከተሉት አላማዎች ሊሰበስቡ ይችላሉ፦
          8.1.1. የተሳታፊውን በፕሮግራሙ ውስጥ ተሳትፎ ለመመዝገብ እና ተሳታፊውን ለመለየት፤
          8.1.2. ድርጅቱና የድርጅቱን አጋሮች ወይም ወኪሎች ፕሮግራሙን በአግባቡ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ተግባራትን ለመፈጸም
          8.1.3. ስለ ፕሮግራሙ ማንኛውንም አስፈላጊ መረጃ ለተሳታፊው ለማሳወቅ
          8.1.4. ሽልማቱን ለተሳታፊው ለማድረስ /ወይም ለማስተላለፍ
          8.1.5. ድርጅቱና የድርጅቱን አጋሮች ወይም ወኪሎች ወደፊት የሚያካሂዷቸውን ፕሮግራሞች ለማሳወቅ፤ ነገር ግን ተሳታፊው በማንኛውም ጊዜ እራሱን ከፕሮግራም ምዝገባ የ መሰረዝ መብት አለው።
        8.2. ህጉ ወይም ስምምነቱ ኩባንያው ያለፈቃድ ግላዊ መረጃውን እንዲሰበስብ ካልፈቀደ በስተቀር ኩባንያው በኩባንያው ዘዴዎች የግል መረጃን ከመሰብሰቡ በፊት ወይም በሚሰበስብበት ጊዜ ከተሳታፊው ፈቃድ ይጠይቃል።
        8.3. ከዚህ በተጨማሪ ድርጅቱ የድርጅቱን አጋሮች ወይም ወኪሎች ጨምሮ ስም፣ ምስል (ምስል እና በካሜራ፣ ሞባይል ስልክ እና ቪዲዮ የሚቀረፁ ተንቀሳቃሽ ምስሎች)፣ ድምፅ እና ማንኛውም ሌላ የተሳታፊዎች መረጃ እና የማታወቂያ አሸናፊዎችን እና የድርጅቱን የህዝብ ግንኙነቶች እና/ወይም ሌላ የድርጅቱ መገናኛ ብዙሃን እንደአስፈላጊነቱ ያለ ጊዜ እና ስፍራ ገደቦች እንዲጠቀም ወይም በድርጅቱ በተገለጸው ማንኛውም ይዘት ለንግድ ስራ ጥቅሞች ለተሳታፊዎች ወይም አሸናፊዎች ምንም አይነት ካሳ መክፈል ሳያስፈልገው ከዚህ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ወይም ከዚህ ውጪ ለሆነ ጉዳይ ለመጠቀም ፈቃድ ሰጥተዋል፡፡
    9. 9. ገዢ ህግ
      1. 9.1. የፕሮግራሙ ውሎች እና ሁኔታዎች በኢትዮጵያ ህግ መሰረት መመራት እና መተርጎም አለባቸው። ተሳታፊው በፕሮግራሙ ውስጥ ከመሳተፉ በፊትም ሆነ በኋላ ወይም በህገ-ወጥ መንገድ ወይም ሌሎች አካላትን ለሚጥስ ማንኛውም ተሳትፎ እና/ወይም ተግባር ቢሳተፍ ድርጂቱ ሃላፊነት የለበትም።
    10. 10. ወጭዎች፦
      1. 10.1. ከፕሮግራሙ ጋር የተያያዙ ወይም በፕሮግራሙ ውስጥ ለመሳተፍ በተሳታፊው የወጣው ወጪ ሁሉ፣ የፖስታ ክፍያዎች የትራንስፖርት ወጪዎች፣ የግንኙነት ክፍያዎች፣ የኤስኤምኤስ ክፍያዎች፣ በሙሉ በተሳታፊው ይሸፈናሉ። ድርጅቱ ተሳታፊውን ለሚያወጣው ወጪ ለመመለስ ማንኛውንም ግዴታ አይኖርበትም።