'የ Double A ኢትዮጵያ ግላዊነት ፖሊሲ

የተሳታፊዎች እና / ወይም የአሸናፊዎች የግል መረጃ ሂደት

  1. ተሳታፊዎች እና / ወይም አሸናፊዎች (“አባል”) አምነው እና ተረድተው Double A (1991) Public Company (“ድርጅቱ”) አባሉ የሰጠውን የግል መረጃዎች ማለትም የመጀመሪያ ስም፤ የአባት ስም፤ ስልክ ቁጥር፤ የመኖሪያ/የስራ አድራሻና አካባቢ ፤ የትውልድ ዘመን ፤ ፆታ ፤ የመታወቅያ ቁጥር እና የኢሜል አድራሻ ቀጥሎ ለተጠቀሱት አላማዎች ሰብስቧል ፣ ተጠቀሟል ወይም አጋርቷል፡፡
    1. በ Double A QR ሽልማት ዕጣ (“ዝግጅት”) ውስጥ ለመሳተፍ እና የአባላቱን ማንነት ለማረጋገጥ።
    2. ከድርጂቱ ወደ አባላቱ ሽልማቶችን ለማድረስ ፡፡
    3. ስለ ዝግጅቱ አስፈላጊ መረጃዎችን ለማሳወቅ ፡፡
    4. አባላቱ በዝግጅቱ ውስጥ በሚሳተፉበት ጊዜ ሁሉ ዝግጅቱን ለማካሄድ አስፈላጊ እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን ፡፡
  2. ድርጅቱ አባሉ በዝግጅቱ ወቅት ተሳተፎውን ሲሰርዝ ወይም ዝግጅቱ ሲጠናቀቅ፤ የግል መረጃውን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ያስወግዳል ፡፡
  3. ድርጅቱ የአባላቱን ስምምነት ካገኘ ድርጅቱን እና ምርቶቹን ለማስተዋወቂያ የአባልን ፎቶ ፣ ቪዲዮ እና ስም መቅዳት ፣ መሰብሰብ ፣ መጠቀም ወይም መግለፅ ይችላል፡፡ ለተጠቀሱት ዓላማዎች ሲባል ድርጅቱ የግል መረጃውን ለኩባንያው ተባባሪዎች ፣ ለሥራ ተቋራጭ ወይም ለአገልግሎት አቅራቢዎች ሊያጋራ ይችላል፡፡
  4. አባላቱ የግል መረጃን ስለ መሰብሰብ ፣ ስለመጠቀም እና ስለማሳወቅ ወይም ፈቃዱን መሻርን በተመለከተ ድርጅቱን ማነጋገር ይችላሉ-
  5. የመረጃ ተቆጣጣሪ፡ Double A (1991) Public Company Limited
    Address: 187/3 Moo 1, Bangna-Trad Km. 42 Road, Bangwua, Bangpakong, Chachoengsao 24180, Thailand.
    Email: ethiopiaQR@doublea1991.com

    በተጨማሪም አባላቱ የድርጅቱን የግል መረጃ ጥበቃ ፖሊሲ ተገቢ መረጃ በ https://www.doubleapaper.com/privacy-policy ማግኘት ይችላሉ ፡፡

የግል መረጃን የመሰብሰብ ፈቃድ

ይህ ስምምነት በ Double A (1991) Public Company Limited (“ድርጅቱ”) እና በ ሽልማቱ ተሳታፊዎች ወይም አሸናፊዎች (“አባል”) መካከል የግል መረጃን ለመሰብሰብ፣ ለመጠቀም እና ይፋ ለማድረግ በድርጅቱ ፖሊሲ መሰረት የተደረገ ነው፡፡ አባሉ ለድርጅቱ የግል መረጃውን ማለትም የመጀመሪያ ስም፤ የአባት ስም፤ ስልክ ቁጥር፤ የመኖሪያ/የስራ አድራሻና አካባቢ፤ ስራ እንዲሰበስብ፤ እንዲጠቀም እና ይፋ እንዲያድረግ የግል መረጃ ጥበቃ ስምምነቱን ቀጥሎ በተጠቀሰው ውሎች እና ሁኔታዎች መሰረት ይሰጣል፡፡

  1. የግል መረጃው የሚሰበሰብበት ዓላማ
    1. ስለድርጅቱ አገልግሎት ፣ ግንኙነት እና መረጃ ለመስጠት ፡፡
    2. ለሽያጭ እና ለገበያ እንቅስቃሴዎች መረጃን ለመተንተን እና የድርጅቱን ምርት እና አገልግሎት ለማልማት ፡፡
    3. ለተጠቀሱት ና አባሉ ለተስማማባቸው አላማዎች፤ አባሉ ድርጂቱ የግል መረጃውን ለ አጋሮችና አገልግሎት ሰጪዎች በተፈቀደው ጊዜ ውስጥ እንዲያጋራ ፈቅዱአል፡፡

  2. የአባሉ መብት

    አባሉ በድርጅቱ የግል መረጃ ጥበቃ ፖሊሲ መሠረት የግል መረጃን መድረስ ፣ ማረም ፣ መሰረዝን ጨምሮ የግል መረጃን በተመለከተ ስምምነትን እና ሌሎች መብቶችን የማስወገድ መብት አለው ፡፡ ድርጅቱ አባሉ በዝግጅቱ ወቅት ተሳተፎውን ሲሰርዝ ወይም ዝግጅቱ ሲጠናቀቅ፤ የግል መረጃውን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ያስወግዳል ፡፡

  3. አባሉ ከላይ ለተጠቀሰው ዓላማ (ዎች) የተሰጠውን ስምምነት ካቋረጠ ድርጅቱ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ያካሂዳል ፡፡ ሆኖም ፣ መሰረዙ በዝግጂቱ መሳተፍ እና የግል መረጃን አሠራር ላይ ተጽዕኖ የለውም።

    የመረጃ ተቆጣጣሪ፡ Double A (1991) Public Company Limited
    Address: 187/3 Moo 1, Bangna-Trad Km. 42 Road, Bangwua, Bangpakong, Chachoengsao 24180, Thailand.
    Email: ethiopiaQR@doublea1991.com

    በተጨማሪ፡ አባሉ የድርጅቱን የግል መረጃ ጥበቃ ፖሊሲ ላይ አግባብነት ያለው መረጃ በ https://www.doubleapaper.com/privacy-policy ድህረገፅ ላይ ማግኘት ይችላል፡፡ አባሉ ከላይ ያሉትን ውሎች እና ሁኔታዎች አንብቦ ፣ ተረድቶ ፣ ተስማምቷል። አባሉ ለድርጅቱ ያቀረበው የግል መረጃ እውነተኛ እና ትክክለኛ መሆኑን ያረጋግጣል።

ተስማምቻለሁ